@fdrehopr
ID: 4296998962
linkhttp://www.hopr.gov.et calendar_today27-11-2015 14:12:44
659 Tweet
50,50K Followers
1 Following
5 hours ago
🔥The 9th Round of Easy Loan, Earn $40 Reward is in progress❗️ ⏰ Promotion Period: January 15th - Feburary 15th, 2025 👉 Register now and check more details at gate.io/campaigns/358
2 months ago
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ያቀረቡትን የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ የበጀት መግለጫ አዳምጧል እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት 1. 93 ትሪሊዮን ብር ሆኖ ቀርቧል።
ምክር ቤቱ የዕፅዋት ጥበቃና ኳራንታይን ረቂቅ አዋጅን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል። ረቂቁ ዘርፉን ለማዘመን፣ መጤ እና ወራሪ ተባዮችን ለመከላከል፣ በዘርፉ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ረቂቁ ትልቅ ፋይዳ አለው ተብሏል።
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ። ረቂቁ ዜጎቻችን በውጭ ሀገር ለስራ ሲሰማሩ መብታቸው፣ ጥቅማቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 37ኛ መደበኛ ስብሰባው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበውን ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል፡፡
ምክር ቤቱ ባካሄደው ጉባኤ የስታርትአፕ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።
ዛሬ በተካሄደው ምክር ቤቱ 38ኛ መደበኛ ስብሰባ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በምክር ቤቱ ውይይት ተደርጎበታል። ባለፉት 11 ወራት ከጠቅላላው የወጪ ንግድ 7.21 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል።
a month ago
ምክር ቤቱ ባካሄደው 39ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የመንግስት መስሪያ ቤቶች 2016 በጀት ዓመት የሂሳብ የፋይናንሽያል ህጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን ገምግሟል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ተደጋጋሚ የኦዲት ግኝት በሚታይባቸው ተቋማት ላይ የምክር ቤቱን አሰራር ተከትሎ በቀጣዩ 2018 ዓ.ም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል፡፡
ምክር ቤቱ በ40ኛ መደበኛ ስብሰባው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርትን በማድመጥ ውይይት አደረገ።
ዛሬ በተካሄደው የምክር ቤቱ 41ኛ መደበኛ ስብሰባ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የሚያስችል አዲስ መርሀ ግብር እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡
6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ41ኛ መደበኛ ስብሰባው በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ በዝርዝር ተወያይቷል፡፡
የ2018 የፌዴራል መንግሥት በጀት 1 ነጥብ 93 ትሪሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡
ምክር ቤቱ ባካሄደው በ42ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዶ/ር ለአባላት ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የበለፀገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችንና ለመጭው ትውልዱ ለማስረከብ በሁሉም ዘርፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገለፁ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተያዘዉን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እቅድ ለማሳካት ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ ጥሪ አቀረቡ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ሁለተኛ ልዩ ስብሰባው ሁለት የብድር ስምምነቶችን አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 2ኛ ልዩ ስብሰባው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር ዕይታ ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በ3ኛ ልዩ ጉባኤው "የዜጎችን ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላል" በሚል ሲያከራክር የቆየው ድንጋጌ ማሻሻያ ተደረገበት።
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ምክር ቤቱ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን አከናውኗል ሲሉ ገለፁ፡፡ የምክር ቤቱን የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን ሪፖርትን በ3ኛ ልዩ ሰብሰባው አድምጧል፡፡