Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile
Ethiopia Insider

@ethiopiainsider

Latest news, updates, insights, analysis, features, photos and videos from Ethiopia
Facebook - facebook.com/ethiopiainside…

ID: 1166455374863622153

linkhttp://www.ethiopiainsider.com calendar_today27-08-2019 21:00:47

3,3K Tweet

36,36K Followers

0 Following

Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

በእነ ጌታቸው ረዳ የተመሰረተ አዲስ ክልላዊ ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፍቃድ አገኘ። አዲሱ ፓርቲ “ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ” (ስምረት) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። 🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16013/ #GetachewReda #Solidarity

በእነ ጌታቸው ረዳ የተመሰረተ አዲስ ክልላዊ ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፍቃድ አገኘ። አዲሱ ፓርቲ “ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ” (ስምረት) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።  

🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16013/

#GetachewReda #Solidarity
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ከኢትዮጵያ ከተሞች መካከል በውሃ አቅርቦት “በጣም ትልቅ ችግር” ያለው በሻሸመኔ እንደሆነ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ገለጹ።በሀገሪቱ ያለውን የውሃ ሽፋን በቀጣዮቹ 5 ዓመታት 100% ለማድረስ መታቀዱንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። 🔴➡️ethiopiainsider.com/2025/16025/

ከኢትዮጵያ ከተሞች መካከል በውሃ አቅርቦት “በጣም ትልቅ ችግር” ያለው በሻሸመኔ እንደሆነ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ገለጹ።በሀገሪቱ ያለውን የውሃ ሽፋን በቀጣዮቹ 5 ዓመታት 100% ለማድረስ መታቀዱንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

🔴➡️ethiopiainsider.com/2025/16025/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት አዋጅ በ4 ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ተሻሻለ። የአዋጅ ማሻሻያው ዜጎች “መብታቸው፣ ደህንነታቸው እና ክብራቸው በዘላቂነት መጠበቁን ለማረጋገጥ” “እንዲያስችል ሆኖ የተዘጋጀ ነው” ተብሏል። ለዝርዝሩ ➡️ethiopiainsider.com/2025/16038/

የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት አዋጅ በ4 ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ተሻሻለ። የአዋጅ ማሻሻያው ዜጎች “መብታቸው፣ ደህንነታቸው እና ክብራቸው በዘላቂነት መጠበቁን ለማረጋገጥ” “እንዲያስችል ሆኖ የተዘጋጀ ነው” ተብሏል።

ለዝርዝሩ ➡️ethiopiainsider.com/2025/16038/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

በዳኞች ስራ ማቆም ምክንያት ለሳምንት ተዘግተው የነበሩ የመቐለ ከተማ ፍርድ ቤቶች ዛሬ ስራ ጀመሩ። ዳኞቹ ወደ ስራ የተመለሱት፤ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት ከተካሄደ በኋላ መሆኑን የትግራይ ዳኞች ማህበር ገልጿል። ➡️ethiopiainsider.com/2025/16045/

በዳኞች ስራ ማቆም ምክንያት ለሳምንት ተዘግተው የነበሩ የመቐለ ከተማ ፍርድ ቤቶች ዛሬ ስራ ጀመሩ። ዳኞቹ ወደ ስራ የተመለሱት፤ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት ከተካሄደ በኋላ መሆኑን የትግራይ ዳኞች ማህበር ገልጿል።

➡️ethiopiainsider.com/2025/16045/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ኢትዮጵያ እና የአይ ኤም ኤፍ ባለሙያዎች፤ በተራዘመ የብድር አቅርቦት ሶስተኛ ግምገማ ላይ ከስምምነት ደረሱ። ግምገማው በአይ ኤም ኤፍ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ሲጸድቅ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከተቋሙ 260 ሚሊዮን ዶላር ያገኛል። 🔴➡️ethiopiainsider.com/2025/16051/

ኢትዮጵያ እና የአይ ኤም ኤፍ ባለሙያዎች፤ በተራዘመ የብድር አቅርቦት ሶስተኛ ግምገማ ላይ ከስምምነት ደረሱ። ግምገማው  በአይ ኤም ኤፍ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ሲጸድቅ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከተቋሙ 260 ሚሊዮን ዶላር ያገኛል።
 
🔴➡️ethiopiainsider.com/2025/16051/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ከ1,700 በላይ “የጥቃቅን ቡድኖች” የምክክር አጀንዳዎችን መሰነዱን ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። እስከ ዛሬ ድረስ ባለው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ከ200 ሺህ ሰዎች በላይ መሳተፋቸውንም ገልጿል። #NationalDialogue 🔴ለዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16053/

ከ1,700 በላይ “የጥቃቅን ቡድኖች” የምክክር አጀንዳዎችን መሰነዱን ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ። እስከ ዛሬ ድረስ ባለው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ከ200 ሺህ ሰዎች በላይ መሳተፋቸውንም ገልጿል። #NationalDialogue
 
🔴ለዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16053/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የእነ አቶ ጌታቸው ረዳ ፓርቲ በ1 ወር ከአጋማሽ ውስጥ “በትግራይ መስራች ጉባኤዬን አካሄዳለሁ” አለ። ከሰኞ ጀምሮ የአባላት ምልመላ እና የአደረጃጀት ስራዎችን አከናውናለሁ ብሏል። 🔴ለማንበብ፦ ethiopiainsider.com/2025/16063/ 🔴ለቪዲዮ፦ youtu.be/B-oc3qLdRIg

የእነ አቶ ጌታቸው ረዳ ፓርቲ በ1 ወር ከአጋማሽ ውስጥ “በትግራይ መስራች ጉባኤዬን አካሄዳለሁ” አለ። ከሰኞ ጀምሮ የአባላት ምልመላ እና የአደረጃጀት ስራዎችን አከናውናለሁ ብሏል።

🔴ለማንበብ፦ ethiopiainsider.com/2025/16063/ 

🔴ለቪዲዮ፦ youtu.be/B-oc3qLdRIg
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

መጪውን ሀገራዊ ምርጫ “ፈቃጅ” እና “አስቻይ” ሁኔታዎች ባሉባቸው አካባቢዎች ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ምርጫ ቦርድ ገለጸ።የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ፤ ምርጫው ሲቃረብ “በዝርዝር እና በጥልቀት ይታያል” ብሏል። 🔴ለዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16079/

መጪውን ሀገራዊ ምርጫ “ፈቃጅ” እና “አስቻይ” ሁኔታዎች ባሉባቸው አካባቢዎች ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ምርጫ ቦርድ ገለጸ።የሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ፤ ምርጫው ሲቃረብ “በዝርዝር እና በጥልቀት ይታያል” ብሏል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16079/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የመንግስት እና የግል ሰራተኞች ከደመወዛቸው ላይ ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ እንዲያዋጡ የሚያስገድድ የአዋጅ ድንጋጌ ተሰረዘ። ድንጋጌው የተሰረዘው በሰራተኞች ላይ “ተደራራቢ ጫና እንዳያስከትል” በሚል ምክንያት ነው። ዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16093/

የመንግስት እና የግል ሰራተኞች ከደመወዛቸው ላይ ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ እንዲያዋጡ የሚያስገድድ የአዋጅ ድንጋጌ ተሰረዘ። ድንጋጌው የተሰረዘው በሰራተኞች ላይ “ተደራራቢ ጫና እንዳያስከትል” በሚል ምክንያት ነው።

ዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16093/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኤርትራ ጋር “የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባንም” አሉ። ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ የሆኑ የሀገራዊ ጥቅም ጉዳዮች ስታነሳ “ትኩሳታቸው የሚጨምሩ ሀገራት አሉ” ሲሉም ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል። 🔴ለዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16102/

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኤርትራ ጋር “የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባንም” አሉ። ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ የሆኑ የሀገራዊ ጥቅም ጉዳዮች ስታነሳ “ትኩሳታቸው የሚጨምሩ ሀገራት አሉ” ሲሉም ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል። 

🔴ለዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16102/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የፌደራል መንግስት ለ2018 ያዘጋጀው በጀት፤ ከዘንድሮው አኳያ በግማሽ ትሪሊዮን ብር ገደማ ዕድገት ቢያሳይም በዶላር ሲሰላ ከፍተኛ ቅናሽ አስመዘገበ። ለሚቀጥለው ዓመት የተዘጋጀው በጀት 2 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ ነው። 🔴ዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16120/

የፌደራል መንግስት ለ2018 ያዘጋጀው በጀት፤ ከዘንድሮው አኳያ በግማሽ ትሪሊዮን ብር ገደማ ዕድገት ቢያሳይም በዶላር ሲሰላ ከፍተኛ ቅናሽ አስመዘገበ። ለሚቀጥለው ዓመት የተዘጋጀው በጀት 2 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ ነው።

🔴ዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16120/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የኢትዮጵያ ድንበርን የማካለል ስራ “ተቋማዊ ቅርጽ ሰጥቶ” ለማከናወን በዝግጅት ላይ መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ሀገሪቱ ካላት ድንበር “በአግባቡ የተሰመረ እና የተለየው” ከ50 በመቶ በታች ነው ተብሏል። 🔴ለዝርዝሩ ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16124/

የኢትዮጵያ ድንበርን የማካለል ስራ “ተቋማዊ ቅርጽ ሰጥቶ” ለማከናወን በዝግጅት ላይ መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ሀገሪቱ ካላት ድንበር “በአግባቡ የተሰመረ እና የተለየው” ከ50 በመቶ በታች ነው ተብሏል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16124/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ጥቃቱ መፈጸሙን የአካባቢው ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። 🔴 ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16129/

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። ጥቃቱ መፈጸሙን የአካባቢው ባለስልጣናት አረጋግጠዋል።

🔴 ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16129/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ብቻ ሲካሄድ የቆየው የባንክ ስራ አገልግሎት፤ ከዛሬ ጀምሮ ለውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች በይፋ መከፈቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። #Ethiopia 🔴ለዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16188/

ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ብቻ ሲካሄድ የቆየው የባንክ ስራ አገልግሎት፤ ከዛሬ ጀምሮ ለውጪ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች በይፋ መከፈቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። #Ethiopia 

🔴ለዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16188/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

ለሀገር አቋራጭ የህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች የብቃት ምዘና ዳግም ሊሰጥ ነው። ዳግም ምዘናው የትራፊክ አደጋን በመቀነስ ረገድ “መሰረታዊ ለውጥ ያመጣል” የሚል እምነት ተጥሎበታል። #Ethiopia 🔴ለዝርዝሩ ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16192/

ለሀገር አቋራጭ የህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች የብቃት ምዘና ዳግም ሊሰጥ ነው። ዳግም ምዘናው የትራፊክ አደጋን በመቀነስ ረገድ “መሰረታዊ ለውጥ ያመጣል” የሚል እምነት ተጥሎበታል። #Ethiopia

🔴ለዝርዝሩ ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16192/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የመንግስት ገቢን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ “የሞት የሽረት ጉዳይ ነው” ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናገሩ። ሚኒስትሩ “አዲስ የልማት ጥያቄ ለመፍታት ብለን ከብሔራዊ ባንክ የምንበደርበት ሁኔታ አብቅቶለታል” ሲሉም ተደምጠዋል። 🔴➡️ethiopiainsider.com/2025/16204/

የመንግስት ገቢን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ “የሞት የሽረት ጉዳይ ነው” ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናገሩ። ሚኒስትሩ “አዲስ የልማት ጥያቄ ለመፍታት ብለን ከብሔራዊ ባንክ የምንበደርበት ሁኔታ አብቅቶለታል” ሲሉም ተደምጠዋል።

🔴➡️ethiopiainsider.com/2025/16204/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

የትግራይ ክልል “ወደ ጦርነት እንዳይገባ” የሃይማኖት አባቶች፣ ባለሃብቶች፣ ምሁራን እና ኤምባሲዎች ሚናቸውን “በፍጥነት” እንዲወጡ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ። በክልሉ ውጊያ ቢቀሰቀስ “ዓለም ደንታ የለውም” ብለዋል። 🔴➡️ethiopiainsider.com/2025/16223/

የትግራይ ክልል “ወደ ጦርነት እንዳይገባ” የሃይማኖት አባቶች፣ ባለሃብቶች፣ ምሁራን እና ኤምባሲዎች ሚናቸውን “በፍጥነት” እንዲወጡ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ። በክልሉ ውጊያ ቢቀሰቀስ “ዓለም ደንታ የለውም” ብለዋል።

🔴➡️ethiopiainsider.com/2025/16223/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መካከል “ስጋት፣ ግጭትን፣ ጥርጣሬን እና አለመተማመንን የሚፈጥር ድርጊት ፈጽሟል” ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ፤ ምርጫ ቦርድ ከምዝገባ እንዲሰርዝ ስልጣን የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ። 🔴➡️ethiopiainsider.com/2025/16239/

በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መካከል “ስጋት፣ ግጭትን፣ ጥርጣሬን እና አለመተማመንን የሚፈጥር ድርጊት ፈጽሟል” ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ፤ ምርጫ ቦርድ ከምዝገባ እንዲሰርዝ ስልጣን የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ።

🔴➡️ethiopiainsider.com/2025/16239/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

በሽፋን ምርመራ ወቅት “ከግድያ በስተቀር” የሚፈጸም ወንጀልን ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርገው አወዛጋቢ ድንጋጌ ተሰረዘ። ድንጋጌው የተሰረዘው አዋጁን “በሰፊው እንዲተረጎም የሚያደርግ ስለሆነ ነው” ተብሏል። #Ethiopia 🔴ዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16248/

በሽፋን ምርመራ ወቅት “ከግድያ በስተቀር” የሚፈጸም ወንጀልን ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርገው አወዛጋቢ ድንጋጌ ተሰረዘ። ድንጋጌው የተሰረዘው አዋጁን “በሰፊው እንዲተረጎም የሚያደርግ ስለሆነ ነው” ተብሏል። #Ethiopia

🔴ዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16248/
Ethiopia Insider (@ethiopiainsider) 's Twitter Profile Photo

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ በአዲስ መዋቅር ስር ሆኖ እንደሚቀጥል አስታወቀች። በአዲሱ መዋቅር የሚቀጥሉት፤ የሰብአዊ እርዳታ፣ ዓለም አቀፍ ጤና እና የምግብ ዋስትና መርሃ ግብሮች እንደሆኑ ተገልጿል። 🔴ለዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16255/

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ በአዲስ መዋቅር ስር ሆኖ እንደሚቀጥል አስታወቀች። በአዲሱ መዋቅር የሚቀጥሉት፤ የሰብአዊ እርዳታ፣ ዓለም አቀፍ ጤና እና የምግብ ዋስትና መርሃ ግብሮች እንደሆኑ ተገልጿል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ ethiopiainsider.com/2025/16255/